Teya Salat
free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

:☀:.♥. ውዷ ሙስሊም እህቴ ሆይ ምን ያህል ለባልሽ ታዛዥ ነሽ? .♥.:☀:


10342908 317637171724013 7423432269456379153 n 1

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። ምስጋና ለአለማት ጌታ ለሆነው ለአሏህ ይገባው።

የአሏህ ሰላምና እዝነት በረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ላይ ፣ በቤተሰቦቻቸው ፣ በሶሃቦቻቸው እንዲሁም የሳቸውን ፈለግ እስከ የውመልቂያማ ድረስ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን።

ሴት ልጅ ከእናት አባቷ ቤት ከወጣችበት እለት አንስቶ በባል ቃልኪዳን ውስጥ ትገባለች። ከዚህም ጐንለጐን ባል ለሚስቱ የሚያስፈልጋትን ሁሉ ኢስላም እንዲያሟላላት ሲያዘው፤ እሷን ደግሞ ለርሱ ታዛዥ እንድትሆን ያዛታል። ይህ ማለት ደግሞ ስብዕናዋን አጥታ ፣ መብቷን ተነጥቃ እንደባሪያ ዝቅ ትበል ማለት አይደለም። እራስን በባል ስር በማድረግ ታዛዥ መሆን ማለት እንጂ መጨቆን ወይም ሃሳብን በነፃነት አለመግለፅ ማለት አይደለም። ይልቁንስ ረዳት በመሆን ሃሳቧን ፣ አስተያየቷን እና ስሜቷን ለባሏ ማካፈል ማለት ነው።

እንዲያውም ብልህ ወንድ ማለት በራሱ ሃሳብ ብቻ ተደግፎ የመጨረሻ ውሳኔ ከመወሰኑ በፊት የሚስቱን ሃሳብና አስተያየት የሚጠይቅ ነው።

ከመብት ጋር በተያያዘ በዘመናችን በርካታ ቤተሰቦች እሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች አሉ እነሱም:- ሴት የወንድ ረዳት አይደለችም ፣ የራሷ ነፃነት እና መብት ያላትናት ፣ የቤት ስራ የሴት የወንድ እየተባለ መለየት የለበትም ወ.ዘ.ተ የሚሉ ናቸው።

ነገር ግን ለአንድ ሙስሊም ሴት ትክክለኛ ክብር እና መብት ኢስላም ከሰጣት ውጭ የሚያስከብራት የለም። የሚገርመው ሴቶች እህቶቻችን ባሎታቻቸውን ሲሰድቡ፤ በአመፅ ቤታቸውን ሲንዱ በአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ላይ እያመፁ መሆኑን አለመረዳታቸው ነው። አንዲት ሙእሚን ሴት እራሷን በባሏ ስር በማድረግ ታዛዥ እምትሆነው ባሏ የሚወዳትና የሚጠነቀቅላት ጥሩ ባል በመሆኑ ነው። ሌላው ቀርቶ ፅኑና ደስተኛ የቤተሰብ ፍቅርን መስርታ መኖርን የምትሻ ሴት የባህሪ ችግር ያለባት ቢሆንም እንኴ እራሷን በባሏ ስር ማድረጓን እና ታዛዥ መሆኗን አትተውም፤ ምክኒያቱም የባልን ሐቅ ምን እንደሆነ የተረዳችናትና።

ለባሏ ታዛዥ እማትሆን ጨቅጫቃ ሚስት ግን የባሏን ባህሪ ችክ የሚልና በቀላሉ የሚበሳጭ እንዲሆን ታረገዋለች።

እንግዲህ አንዲት ሙስሊም ሴት በባሏም ሆነ በአሏህ ዘንድ ተወዳጅ ለመሆን የባሏን የቤት አስተዳዳሪ ሃላፊነት ተቀብላ ለባሏ ታዛዥ መሆን ይኖርባታል።

ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል: <አንድን ሰው ከአሏህ ሌላ ላለ እንዲሰግድ ባዝ ኖሮ ሴትን ለባሏ እንድትሰግድ አዛት ነበር አሉ፤ በመቀጠልም በዚያ ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ ሴት የገጌታዋን ሐቅ አታደርስም የባሏን መብት እስካልፈፀመች ድረስ> ብለዋል።

ይህ ሐዲስ እኛ ሴቶች ምን ያህል የባሎቻችንን ሐቅ መጠበቅ እንዳለብን እና ይህ ካላደረግን የከፋ ቅጣት እንደሚጠብቀን በሚገባ ይጠቁመናል። ስለዚህ እህቶቼ ይህንን አውቀን ተወዳጅ እና የባልን ሐቅ ጠባቂ እንሁን።

አሏህ ላላገባን ጥሩ ትዳርን ላገባችሁ ደግሞ ባሎቻችሁን ተንከባካቢና ታዛዥ ያድርጋችሁ። አሚን!!!

By Nejwa Bint Islam member of Youth-Mission

page:
http://facebook.com/youth.mission29

website:
http://youth-mission.mobie.in

{.♥.° ኑ ስለ ኢስላም እንተዋወስ °.♥.}
'~'-.,__,.-'~'
_,.-'~''~'-.,_
©የወጣቱ ተልእኮ

4459

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ